ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 33:17-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤ከትዕቢት ይጠብቃል፤

18. ነፍሱን ከጒድጓድ፤ሕይወቱንም ከሰይፍ ጥፋት ያድናል።

19. ደግሞም ሰው ታሞ በዐልጋው ላይ ሳለ፣በዐጥንቱ የዘወትር ሥቃይ ይገሥጸዋል፤

20. ያኔም ሕይወቱ መብልን ትጠላለች፤ነፍሱም ምርጥ ምግብን ትጠየፋለች።

21. እንዳልነበረ ሆኖ ሥጋው ይመነምናል፤ተሸፍኖ የነበረው ዐጥንቱም ገጦ ይወጣል።

22. ነፍሱ ወደ ጒድጓድ፣ሕይወቱም ወደ ሞት መልእክተኞች ትቀርባለች።

23. “ሆኖም ትክክለኛውን መንገድ ለሰው ያመለክት ዘንድ፣መካከለኛም ይሆንለት ዘንድ፣ከሺህ አንድ መልአክ ቢገኝ፣

24. ለሰውየውም በመራራት፣‘ቤዛ አግኝቼለታለሁና፣ወደ ጒድጓድ እንዳይወርድ አድነው’ ቢለው፣

25. በዚህ ጊዜ ሥጋው እንደ ሕፃን ልጅ ገላ ይታደሳል፤ወደ ወጣትነቱም ዘመን ይመለሳል።

26. ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፤ ሞገስም ያገኛል፤የእግዚአብሔርን ፊት ያያል፤ ሐሤትም ያደርጋል፤እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ ቦታው ይመልሰዋል።

27. ከዚያም ወደ ሰዎች መጥቶ እንዲህ ይላል፤‘ኀጢአትን ሠርቻለሁ፤ ትክክል የሆነውን አጣምሜአለሁ፤ነገር ግን የእጄን አላገኘሁም።

28. ነፍሴ ወደ ጒድጓድ እንዳትወርድ፣ታድጎአታል፤ በሕይወትም ሆኜ ብርሃን አያለሁ።’

29. “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ፣ሁለት ሦስት ጊዜ ለሰው ያደርጋል።

30. ይኸውም የሕይወት ብርሃን ይበራለት ዘንድ፣ነፍሱን ከጒድጓድ ለመመለስ ነው።

31. “ኢዮብ ሆይ፤ ልብ ብለህ ስማኝ፤እኔ ልናገር፤ አንተ ዝም በል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 33