ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 33:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “አሁን ግን ኢዮብ ሆይ፣ ንግግሬን ስማ፤የምለውንም ሁሉ አድምጥ።

2. እንግዲህ አፌን እከፍታለሁ፤አንደበቴም ይናገራል።

3. ቃሌ ከቅን ልብ ይወጣል፤ከንፈሬም የማውቀውን በትክክል ይናገራል።

4. የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ሁሉን የሚችለውም አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።

5. የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤ተዘጋጅተህም በፊቴ ቁም።

6. በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንዳንተው ነኝ፤የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው።

7. እኔን መፍራት የለብህም፤እጄም ሊከብድብህ አይገባም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 33