ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 32:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብ በበኩሉ ራሱን እንደ ጻድቅ ቈጥሮ ስለ ነበር፣ እነዚህ ሦስት ሰዎች ለእርሱ መልስ መስጠታቸውን ተዉ።

2. ከራም ወገን የሆነው፣ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ግን ኢዮብ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ ስላደረገ፣ እጅግ ተቈጣው።

3. ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች በኢዮብ ላይ መፍረድ እንጂ፣ ነገሩን ሊያሳምኑት ስላልቻሉ፣ በእነርሱም ላይ ተቈጣ።

4. ኤሊሁ፣ ሌሎቹ በዕድሜ ይበልጡት ስለ ነበር ከእነርሱ ቀድሞ ለኢዮብ ሳይናገር ቈየ።

5. ነገር ግን እነዚህ ሦስቱ የሚሉትን ባጡ ጊዜ ቍጣው ነደደ።

6. ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤“እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ፈርቼ ዝም አልሁ።

7. ‘ዕድሜ ይናገራል፤ረጅም ዘመን ጥበብን ያስተምራል’ ብዬ ነበር።

8. ነገር ግን በሰው ያለው መንፈስ፣ሁሉን የሚችል አምላክ እስትንፋስ፣ማስተዋልን ይሰጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 32