ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፤የአሞራም ዐይን አላየውም፣

8. ኵሩ አራዊት አልረገጡትም፤አንበሳም በዚያ አላለፈም።

9. ሰው እጁን በቡላድ ድንጋይ ላይ ያነሣል፤ተራሮችንም ከሥር ይገለብጣል።

10. በድንጋይ ውስጥ መተላለፊያ ያበጃል፤ዐይኖቹም የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያሉ።

11. የወንዞችን ምንጭ ይበረብራል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።

12. “ነገር ግን ጥበብ ከወዴት ትገኛለች?ማስተዋልስ መኖሪያዋ የት ነው?

13. ሰው ዋጋዋን አያውቅም፤በሕያዋንም ምድር አትገኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28