ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የሰው እግር ረግጦት በማያውቅበት ስፍራ፣ከሰዎች መኖሪያ ርቆ መውረጃ ጒድጓድ ይቈፍራል፤ሰው በሌለበት ቦታ ይንጠላጠላል፤ ይወዛወዛል።

5. ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች።

6. ሰንፔር ከዐለቷ ይወጣል፤ከዐፈሯም የወርቅ አንኳር ይገኛል።

7. ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፤የአሞራም ዐይን አላየውም፣

8. ኵሩ አራዊት አልረገጡትም፤አንበሳም በዚያ አላለፈም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28