ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:18-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ዛጐልና አልማዝ ከቍጥር አይገቡም፤የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍም ይበልጣል።

19. የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን ሊስተካከላት አይችልም፤ዋጋዋም በንጹሕ ወርቅ አይተመንም።

20. “ታዲያ፣ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች?ማስተዋልስ የት ትገኛለች?

21. ከሕያዋን ፍጥረታት ዐይን ሁሉ ተሰውራለች፤ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።

22. ጥፋትና ሞት፣‘ወሬዋን ብቻ ሰማን’ ይላሉ።

23. ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ የሚረዳ፣መኖሪያዋንም የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤

24. እርሱ የምድርን ዳርቻ ይመለከታልና፤ከሰማይ በታች ያለውንም ሁሉ ያያል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28