ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በኦፊር ወርቅ፣በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።

17. ወርቅም ብርሌም አይወዳደሯትም፤በወርቅ ጌጥም አትለወጥም።

18. ዛጐልና አልማዝ ከቍጥር አይገቡም፤የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍም ይበልጣል።

19. የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን ሊስተካከላት አይችልም፤ዋጋዋም በንጹሕ ወርቅ አይተመንም።

20. “ታዲያ፣ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች?ማስተዋልስ የት ትገኛለች?

21. ከሕያዋን ፍጥረታት ዐይን ሁሉ ተሰውራለች፤ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28