ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በኦፊር ወርቅ፣በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።

17. ወርቅም ብርሌም አይወዳደሯትም፤በወርቅ ጌጥም አትለወጥም።

18. ዛጐልና አልማዝ ከቍጥር አይገቡም፤የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍም ይበልጣል።

19. የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን ሊስተካከላት አይችልም፤ዋጋዋም በንጹሕ ወርቅ አይተመንም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28