ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “የብር ማዕድን የሚወጣበት፣ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።

2. ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል።

3. ሰው፣ እስከ ጨለማ መጨረሻ ይዘልቃል፤ከድቅድቅ ጨለማ የማዕድን ድንጋይ ለማግኘት፣እስከ ውስጠኛው ዋሻ ገብቶ ይፈልጋል።

4. የሰው እግር ረግጦት በማያውቅበት ስፍራ፣ከሰዎች መኖሪያ ርቆ መውረጃ ጒድጓድ ይቈፍራል፤ሰው በሌለበት ቦታ ይንጠላጠላል፤ ይወዛወዛል።

5. ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28