ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “የብር ማዕድን የሚወጣበት፣ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።

2. ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል።

3. ሰው፣ እስከ ጨለማ መጨረሻ ይዘልቃል፤ከድቅድቅ ጨለማ የማዕድን ድንጋይ ለማግኘት፣እስከ ውስጠኛው ዋሻ ገብቶ ይፈልጋል።

4. የሰው እግር ረግጦት በማያውቅበት ስፍራ፣ከሰዎች መኖሪያ ርቆ መውረጃ ጒድጓድ ይቈፍራል፤ሰው በሌለበት ቦታ ይንጠላጠላል፤ ይወዛወዛል።

5. ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች።

6. ሰንፔር ከዐለቷ ይወጣል፤ከዐፈሯም የወርቅ አንኳር ይገኛል።

7. ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፤የአሞራም ዐይን አላየውም፣

8. ኵሩ አራዊት አልረገጡትም፤አንበሳም በዚያ አላለፈም።

9. ሰው እጁን በቡላድ ድንጋይ ላይ ያነሣል፤ተራሮችንም ከሥር ይገለብጣል።

10. በድንጋይ ውስጥ መተላለፊያ ያበጃል፤ዐይኖቹም የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያሉ።

11. የወንዞችን ምንጭ ይበረብራል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።

12. “ነገር ግን ጥበብ ከወዴት ትገኛለች?ማስተዋልስ መኖሪያዋ የት ነው?

13. ሰው ዋጋዋን አያውቅም፤በሕያዋንም ምድር አትገኝም።

14. ውቅያኖስ፣ ‘በእኔ ውስጥ የለችም’ ይላል፤ባሕርም፣ ‘በእኔ ዘንድ አይደለችም’ ይላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28