ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 17:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ጨልሞም እያዩ፣ ‘ብርሃን ቀርቦአል’ ይላሉ።

13. ተስፋ የማደርገው ቤት መቃብር ብቻ ከሆነ፣መኝታዬንም በጨለማ ካነጠፍሁ፣

14. መበስበስን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ትልንም፣ ‘አንቺ እናቴ’ ወይም ‘እኅቴ ነሽ’ ካልሁ፣

15. ታዲያ፣ የእኔ ተስፋ ወዴት ነው?ተስፋዬን የሚያይልኝስ ማን ነው?

16. ወደ ሞት ደጅ ይወርዳልን?አብረንስ ወደ ትቢያ እንሄዳለንን?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 17