ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 15:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በእግዚአብሔር የመማክርት ጉባኤ ላይ ነበርህን?ጥበብስ የተሰጠው ለአንተ ብቻ ነው?

9. እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ?እኛስ የሌለን አንተ ያለህ ማስተዋል የቱ ነው?

10. በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡ፣የሸበቱ ሽማግሌዎች ከእኛ ጋር አሉ።

11. የእግዚአብሔር ማጽናናት፣በርጋታ የተነገረህ ቃል አነሰህን?

12. ልብህ ለምን ይሸፍታል?ዐይንህንስ ምን ያጒረጠርጠዋል?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 15