ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 15:29-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ከእንግዲህ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይቈይም፤ይዞታውም በምድር ላይ አይሰፋም።

30. ከጨለማ አያመልጥም፤ቅርንጫፎቹን ነበልባል ያደርቃቸዋል፤በእግዚአብሔርም እስትንፋስ ይወሰዳል።

31. በአጸፋው አንዳች አያገኝምና፤ከንቱን ነገር በመታመን ራሱን አያታልል።

32. ጊዜው ሳይደርስ ይጠወልጋል፤ቅርንጫፉም አይለመልምም።

33. ፍሬው በጮርቃነት እንደ ተለቀመበት የወይን ተክል፤አበባውም እንደ ረገፈበት የወይራ ዛፍ ይሆናል።

34. የዐመፀኞች ጉባኤ ትመክናለች፤የጉቦ ሱሰኞችም ድንኳን በእሳት ትበላለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 15