ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 15:13-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. በእግዚአብሔር ላይ እንድትቈጣ፣እንደዚህ ያለ ቃል ከአፍህ እንዲወጣ ያደረገህ ምንድን ነው?

14. “ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው?

15. እነሆ፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ሰማያትም በእርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም።

16. ታዲያ፣ ክፋትን እንደ ውሃ የሚጠጣ!አስጸያፊና ርኩስ ሰውማ እንዴት ይታመን!

17. “አድምጠኝ፤ በግልጽ አስረዳሃለሁ፤ያየሁትንም እነግርሃለሁ፤

18. ጠቢባን ከአባቶቻቸው የተቀበሉትን፤ሳይሸሽጉ የተናገሩትን አስረዳሃለሁ፤

19. ምድሪቱ ለአባቶቻቸው ተሰጠች፤በመካከላቸውም ባዕድ አልተቀመጠም፤

20. ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ፣ጨካኙም በተመደበለት ዘመን ሁሉ ይሠቃያል።

21. የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ላይ ይጮኻል፤በሰላም ጊዜ ቀማኞች አደጋ ያደርሱበታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 15