ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 14:7-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “ዛፍ እንኳ ቢቈረጥ፣እንደ ገና ሊያቈጠቍጥ፣አዳዲስ ቅርንጫፍም ሊያበቅል ተስፋ አለው።

8. ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅጒቶው በመሬት ውስጥ ቢበሰብስም፣

9. የውሃ ሽታ ባገኘ ጊዜ ያቈጠቍጣል፤እንደ ተተከለም ችግኝ ቅርንጫፍ ያወጣል።

10. ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?

11. ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣

12. እንደዚሁም ሰው ይተኛል ቀናም አይልም፤ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ከእንቅልፉም አይነሣም።

13. “ምነው መቃብር ውስጥ በሰወርኸኝ!ቍጣህም እስከሚያልፍ በሸሸግኸኝ!ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!

14. ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል?እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ።

15. ትጠራኛለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 14