ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ከሴት የተወለደ ሰው፣ዘመኑ አጭርና በመከራ የተሞላ ነው፤

2. እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም።

3. እንደዚህ ባለ ሰው ላይ ዐይንህን ታሳርፋለህን?ለፍርድስ በፊትህ ታቀርበዋለህን?

4. ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹሕን ማን ሊያወጣ ይችላል?አንድ እንኳ የሚችል የለም!

5. የሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፣የወራቱንም ብዛት ወስነህ አስቀምጠሃል፤ሊያልፈው የማይችለውንም ገደብ አኖርህለት።

6. እንግዲህ ዘመኑን እንደ ምንደኛ እስኪፈጽም ድረስ፣ፊትህን ከእርሱ መልስ፤ ተወው።

7. “ዛፍ እንኳ ቢቈረጥ፣እንደ ገና ሊያቈጠቍጥ፣አዳዲስ ቅርንጫፍም ሊያበቅል ተስፋ አለው።

8. ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅጒቶው በመሬት ውስጥ ቢበሰብስም፣

9. የውሃ ሽታ ባገኘ ጊዜ ያቈጠቍጣል፤እንደ ተተከለም ችግኝ ቅርንጫፍ ያወጣል።

10. ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?

11. ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣

12. እንደዚሁም ሰው ይተኛል ቀናም አይልም፤ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ከእንቅልፉም አይነሣም።

13. “ምነው መቃብር ውስጥ በሰወርኸኝ!ቍጣህም እስከሚያልፍ በሸሸግኸኝ!ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!

14. ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል?እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ።

15. ትጠራኛለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ።

16. በዚያን ጊዜ በእርግጥ እርምጃዬን ትከታተላለህ፤ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም።

17. መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።

18. “ተራራ እንደሚሸረሸርና እንደሚወድቅ፣ዐለትም ከስፍራው እንደሚወገድ፣

19. ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ጐርፍም ዐፈርን አጥቦ እንደሚወስድ፣አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ።

20. አንድ ጊዜ ፈጽመህ ትበረታለህ፤ እርሱም ያልፋል፤ገጽታውን ትቀይራለህ፤ ትሸኘዋለህም።

21. ልጆቹ ቢከበሩ አያውቅም፤ቢዋረዱም አያይም።

22. የገዛ አካሉ ሕመም ብቻ ይሰማዋል፤ለራሱም ብቻ ያለቅሳል።”