ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 12:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “በእርግጥ ሰው ማለት እናንተ ናኋ!ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ!

3. ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ አእምሮ አለኝ፤ከእናንተ አላንስም፤እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው?

4. እግዚአብሔርን ጠርቼ የመለሰልኝ ሰው ብሆንም፣ለባልንጀሮቼ መሣቂያ ሆኛለሁ፤ጻድቅና ያለ ነቀፋ ሆኜ እያለሁ፣ መሣቂያ ሆኛለሁ።

5. የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ።

6. የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።

7. “እስቲ እንስሶችን ጠይቁ፤ ያስተምሯችኋል፤የሰማይ ወፎችንም ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 12