ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢዮብ

1. ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “በእርግጥ ሰው ማለት እናንተ ናኋ!ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ!

3. ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ አእምሮ አለኝ፤ከእናንተ አላንስም፤እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው?

4. እግዚአብሔርን ጠርቼ የመለሰልኝ ሰው ብሆንም፣ለባልንጀሮቼ መሣቂያ ሆኛለሁ፤ጻድቅና ያለ ነቀፋ ሆኜ እያለሁ፣ መሣቂያ ሆኛለሁ።

5. የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ።

6. የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።

7. “እስቲ እንስሶችን ጠይቁ፤ ያስተምሯችኋል፤የሰማይ ወፎችንም ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤

8. ለምድር ተናገሩ፤ ታስተምራችኋለች፤የባሕርም ዓሣ ይነግራችኋል።

9. የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማን ነው?

10. የፍጥረት ሁሉ ሕይወት፣የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና፤

11. ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ጆሮ ቃላትን አይለይምን?

12. ጥበብ ያለው በአረጋውያን ዘንድ አይደለምን?ማስተዋልስ ረጅም ዕድሜ ባላቸው ዘንድ አይገኝምን?

13. “ጥበብና ኀይል የእግዚአብሔር ናቸው፤ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ።

14. እርሱ ያፈረሰውን መልሶ የሚገነባ የለም፣እርሱ ያሰረውን የሚፈታ አይገኝም።

15. እርሱ ውሃን ቢከለክል፣ ድርቅ ይሆናል፤ቢለቀውም ውሃው ምድሪቱን ያጥለቀልቃል።

16. ብርታትና ድል ማድረግ በእርሱ ዘንድ ይገኛል፤አታላዩም ተታላዩም በእርሱ እጅ ናቸው።

17. አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል።

18. ነገሥታትን ድግ ያስፈታል፤ገመድም በወገባቸው ያስራል።

19. ካህናትን ከክህነታቸው ያዋርዳል፤ለዘመናት የተደላደሉትንም ይገለብጣል።

20. ዕውቅ መካሪዎችን ቋንቋ ያሳጣል፤የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስዳል።

21. የተከበሩትን ውርደት ያከናንባል፤ብርቱዎችንም ትጥቅ ያስፈታል።

22. የጨለማን ጥልቅ ነገሮች ይገልጣል፤የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።

23. ሕዝቦችን ታላቅ ያደርጋል፤ መልሶም ያጠፋቸዋል፤ሕዝቦችን ያበዛል፤ ያፈልሳቸዋልም።

24. የዓለም መሪዎችን ማስተዋል ይነሣል፤መንገድ በሌለበት በረሓም ያቅበዘብዛቸዋል፤