ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 11:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. መጠኑ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።

10. “እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል?

11. በእውነት እርሱ ሸፍጠኞችን ያውቃል፣ክፋት ሲሠራም ልብ ይላል።

12. ጅል ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ፣የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።

13. “ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣

14. በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣

15. በዚያን ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 11