ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሶፋር

1. ነዕማታዊው ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ይህ ሁሉ ቃል መልስ ማግኘት አይገባውምን?ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ እውነተኛ ይቈጠርን?

3. በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን?ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም?

4. እግዚአብሔርንም፣ ‘ትምህርቴ የጠራ፤በዐይንህም ፊት የጸዳሁ ነኝ’ ትለዋለህ።

5. ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት!

6. እውነተኛ ጥበብ ባለ ብዙ ፈርጅ ናትና፣የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ!እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።

7. “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን?ወይስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?

8. ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ?ከሲኦልም ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?

9. መጠኑ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።

10. “እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል?

11. በእውነት እርሱ ሸፍጠኞችን ያውቃል፣ክፋት ሲሠራም ልብ ይላል።

12. ጅል ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ፣የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።

13. “ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣

14. በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣

15. በዚያን ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤

16. መከራህን ትረሳለህ፤ዐልፎ እንደሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ።

17. ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፤ጨለማውም እንደ ንጋት ይሆናል።

18. ተስፋ ስላለ ተደላድለህ ትቀመጣለህ፤ዙሪያህን ትመለከታለህ፤ በሰላምም ታርፋለህ።

19. ያለ አንዳች ሥጋት ትተኛለህ፤ብዙ ሰዎችም ደጅ ይጠኑሃል።

20. የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለችማምለጫም አያገኙም፤ተስፋቸውም ሞት ብቻ ነው።”