ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 11:5-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት!

6. እውነተኛ ጥበብ ባለ ብዙ ፈርጅ ናትና፣የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ!እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።

7. “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን?ወይስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?

8. ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ?ከሲኦልም ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?

9. መጠኑ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።

10. “እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል?

11. በእውነት እርሱ ሸፍጠኞችን ያውቃል፣ክፋት ሲሠራም ልብ ይላል።

12. ጅል ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ፣የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።

13. “ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣

14. በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣

15. በዚያን ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 11