ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 11:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነዕማታዊው ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ይህ ሁሉ ቃል መልስ ማግኘት አይገባውምን?ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ እውነተኛ ይቈጠርን?

3. በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን?ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም?

4. እግዚአብሔርንም፣ ‘ትምህርቴ የጠራ፤በዐይንህም ፊት የጸዳሁ ነኝ’ ትለዋለህ።

5. ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት!

6. እውነተኛ ጥበብ ባለ ብዙ ፈርጅ ናትና፣የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ!እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 11