ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 11:21-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. በዚያን ጊዜ ኢያሱ ሄዶ በተራራማው አገር ማለት በኬብሮን፣ በዳቤርና በአናብ እንዲሁም በመላው የይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን የዔናቅን ዘሮች ከነከተሞቻቸው በሙሉ ደመሰሳቸው፤

22. ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፣ በጌትና በአሽዶድ ሲቀሩ፣ በእስራኤል የቀሩ የዔናቅ ዘሮች ግን አልነበሩም።

23. ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን በሙሉ ያዘ፤ እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው።ከዚያም ምድርቱ ከጦርነት ዐረፈች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 11