ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 9:4-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው፣የከበዳቸውን ቀንበር፣በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

5. የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ለእሳት ይዳረጋል፤ይማገዳልም።

6. ሕፃን ተወልዶልናልና፤ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ኀያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

7. ለመንግሥቱ ስፋት፣ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናትይህን ያደርጋል።

8. ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።

9. ሕዝቡ በሙሉ፣ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎችይህን ያውቃሉ፤በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤

10. “ጡቦቹ ወድቀዋል፤እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”

11. ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል።

12. ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫ ጭቋታል።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።

13. ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።

14. ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸምበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 9