ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 65:4-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በመቃብር መካከል የሚቀመጡ፣በስውር ቦታዎች የሚያድሩ፣የዕሪያ ሥጋ የሚበሉ፣ማሰሮዎቻቸውን በረከሰ ሥጋ መረቅ የሚሞሉ ናቸው፤

5. ‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ’ የሚሉ ናቸው።እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።

6. “እነሆ፤ እንዲህ የሚል ተጽፎ በፊቴ ተቀምጦአል፤ዝም አልልም፤ ነገር ግን እንደ ሥራው እሰጠዋለሁ፤የእጃቸውንም እከፍላቸዋለሁ፤

7. የእናንተን ኀጢአት የአባቶቻችሁንም ኀጢአት እበቀላለሁ”ይላል እግዚአብሔር።“በተራሮች ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ስላቀረቡ፣በኰረብቶች ላይ ስለ ሰደቡኝ፣በሰፈሩት ቊና ይሰፈርባቸዋል፤ስለ ቀደሙት ሥራዎቻቸውም የእጃቸውን ያገኛሉ።”

8. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በወይኑ ዘለላ ውስጥ ጭማቂው ገና እንዳለ ሁሉ፣ሰዎችም፣ ‘በውስጡ ጥሩ ነገር ስላለአትቊረጡት’ እንደሚሉ፣እኔም ስለ ባሮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።

9. ከያዕቆብ ዘር የሆኑትን፣ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሱትን አመጣለሁ።የተመረጠው ሕዝቤ ይወርሳቸዋል፤ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።

10. አጥብቀው ለሚፈልጉኝ ሕዝቤ፣ሳሮን የበጎች መሰማሪያ፣የአኮር ሸለቆም የከብቶች ማረፊያ ይሆናል።

11. “ነገር ግን እግዚአብሔርን ለተዋችሁት ለእናንተ፣የተቀደሰ ተራራዬን ለረሳችሁት፣‘ዕጣ ፈንታ’ ለተባለ ጣዖት ቦታ ላዘጋጃችሁት፣‘ዕድል’ ለተባለም ጣዖት ድብልቅ የወይን ጠጅ በዋንጫ ለሞላችሁት፣

12. ተጣርቼ ስላልመለሳችሁ፣ተናግሬ ስላልሰማችሁ፣በፊቴ ክፉ ነገር ስላደረጋችሁ፣የሚያስከፋኝን ነገር ስለ መረጣችሁ፣ለሰይፍ እዳርጋችኋለሁ፤ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ።”

13. ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ባሮቼ ይበላሉ፤እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ባሮቼ ይጠጣሉ፤እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ባሮቼ ደስ ይላቸዋል፤እናንተ ግን ታፍራላችሁ።

14. ባሮቼ፣ከልብ በመነጨ ደስታ ይዘምራሉ፤እናንተ ግን፣ልባችሁ በማዘኑ ትጮኻላችሁ፤መንፈሳችሁ በመሰበሩም ወዮ ትላላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 65