ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 65:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ላልለመኑኝ ራሴን ገለጥሁላቸው፤ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው።ስሜን ላልጠራ ሕዝብ፣‘አለሁልህ፤ አለሁልህ’ አልሁት።

2. ለዐመፀኛ ሕዝብ፣መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ።ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣

3. በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤

4. በመቃብር መካከል የሚቀመጡ፣በስውር ቦታዎች የሚያድሩ፣የዕሪያ ሥጋ የሚበሉ፣ማሰሮዎቻቸውን በረከሰ ሥጋ መረቅ የሚሞሉ ናቸው፤

5. ‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ’ የሚሉ ናቸው።እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።

6. “እነሆ፤ እንዲህ የሚል ተጽፎ በፊቴ ተቀምጦአል፤ዝም አልልም፤ ነገር ግን እንደ ሥራው እሰጠዋለሁ፤የእጃቸውንም እከፍላቸዋለሁ፤

7. የእናንተን ኀጢአት የአባቶቻችሁንም ኀጢአት እበቀላለሁ”ይላል እግዚአብሔር።“በተራሮች ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ስላቀረቡ፣በኰረብቶች ላይ ስለ ሰደቡኝ፣በሰፈሩት ቊና ይሰፈርባቸዋል፤ስለ ቀደሙት ሥራዎቻቸውም የእጃቸውን ያገኛሉ።”

8. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በወይኑ ዘለላ ውስጥ ጭማቂው ገና እንዳለ ሁሉ፣ሰዎችም፣ ‘በውስጡ ጥሩ ነገር ስላለአትቊረጡት’ እንደሚሉ፣እኔም ስለ ባሮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 65