ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 60:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የመንግሥታትን ወተት ትጠጫለሽ፤የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደሆንሁ ታውቂያለሽ።

17. በናስ ፈንታ ወርቅ፣በብረትም ፈንታ ብር አመጣልሻለሁ።ሰላምን ገዥሽ፣ጽድቅንም አለቃሽ አደርጋለሁ።

18. ከእንግዲህ በምድርሽ ሁከት፣በጠረፎችሽም ጥፋትና መፈራረስ አይሰማም፤ነገር ግን ቅጥሮችሽን ድነት፣በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 60