ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 59:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እነሆ፤ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፤ጆሮውም መስማት አልተሳናትም

2. ነገር ግን በደላችሁከአምላካችሁ ለይቶአችኋል፤ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤በዚህም ምክንያት አይሰማም።

3. እጆቻችሁ በደም፣ጣቶቻችሁ በበደል ተነክረዋል፤ከንፈሮቻችሁ ሐሰትን ተናገሩ፤ምላሶቻችሁ ክፉ ነገርን አሰሙ።

4. ፍትሕን የሚጠራ ማንም የለም፤ጒዳዩን በቅንነት የሚያቀርብ የለም፤በከንቱ ነገር ታመኑ፤ ሐሰትን ተናገሩ፤ሁከትን ፀነሱ፤ ክፋትንም ወለዱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 59