ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 58:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ‘አንተ ካልተቀበልኸው፣ስለ ምን ብለን ጾምን?አንተ ከጒዳይ ካልቈጠርኸው፣ስለ ምን ራሳችንን አዋረድን?’ ይላሉ።“ሆኖም በጾማችሁ ቀን የልባችሁን ታደርጋላችሁ፤ሠራተኞቻችሁንም ትበዘብዛላችሁ።

4. ጾማችሁ በጥልና በክርክር፣በግፍ ጡጫና በመደባደብ ይፈጸማል፤ከእንግዲህ ዛሬ እንደምትጾሙት ጾማችሁ፣ድምፃችሁ ወደ ላይ እንደሚሰማም ተስፋ አታድርጉ።

5. እኔ የመረጥሁት ጾም እንዲህ ዐይነቱን ነውን?ሰውስ ራሱን የሚያዋርደው በእንዲህ ያለው ቀን ብቻ ነውን?እንደ ደንገል ራስን ዝቅ ማድረግ ነውን?ወይስ ማቅ ለብሶ በዐመድ ላይ መንከባለል ነውን?ታዲያ ጾም ብለህ የምትጠራው ይህን ነውን? እግዚአብሔርስ የሚቀበለው እንዲህ ያለውን ቀን ነውን?

6. “እንግዲህ እኔ የመረጥሁት ጾም፣የጭቈናን ሰንሰለት እንድትበጥሱ፣የቀንበርን ገመድ እንድትፈቱ፣የተጨቈኑትን ነጻ እንድታወጡ፣ቀንበርን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን?

7. ምግብህን ለተራበ እንድታካፍለው፣ተንከራታቹን ድኻ ወደ ቤትህ እንድታስገባው፣የተራቈተውን ስታይ እንድታለብሰው፣የሥጋ ዘመድህንም ፊት እንዳትነሣው አይደለምን?

8. ይህ ከሆነ ብርሃንህ እንደ ንጋት ጮራ ይፈነጥቃል፤ፈውስህ ፈጥኖ ይደርሳል፤ጽድቅህ ቀድሞህ ይሄዳል፤ የእግዚአብሔር ክብር ደጀን ይሆንልሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 58