ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 57:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የሰው መንፈስ በፊቴ እንዳይዝል፣የፈጠርሁትም ሰው እስትንፋስ እንዳይቆም፣ለዘላለም አልወቅስም፤ሁልጊዜም አልቈጣም።

17. ኀጢአት ስለ ሞላበት ስግብግብነቱ ተቈጣሁት፤ቀጣሁት፤ ፊቴንም በቍጣ ከእርሱ ሸሸግሁ፤ያም ሆኖ በገዛ መንገዱ ገፋበት።

18. መንገዶቹን አይቻለሁ፤ ቢሆንም እፈውሰዋለሁ፤እመራዋለሁ፤ ለእርሱና ስለ እርሱ ለሚያለቅሱትምመጽናናትን እመልሳለሁ፤

19. በእስራኤል አልቃሾች ከንፈር ላይ ምስጋና እፈጥራለሁ።በቅርብና በሩቅ ላሉት ሰላም፣ ሰላም ይሁን፤እኔ እፈውሳቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

20. ክፉዎች ግን ማዕበሉ ጭቃና ጒድፍ እንደሚያወጣ፣ጸጥ ማለት እንደማይችል፣እንደሚናወጥ ባሕር ናቸው።

21. አምላኬ፣ “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 57