ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 53:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር።ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።

4. በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ሕመማችንንም ተሸከመ፤እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው።

5. ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ስለ በደላችንም ደቀቀ፤በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6. እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደልበእርሱ ላይ ጫነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 53