ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 52:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እናንት የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአል፤ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቶአልና።

10. እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣የተቀደሰ ክንዱን ይገልጣል፤በምድር ዳርቻዎች ያሉ ሁሉ፣የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።

11. እናንት የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣ተለዩ፤ ተለዩ፤ ከዚያ ውጡ፤ርኵስ ነገር አትንኩ፤ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ።

12. ሆኖም በችኰላ አትወጡም፤ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ እግዚአብሔር ፊት ፊታችሁ ይሄዳል፤የእስራኤል አምላክ ደጀን ይሆናችኋል።

13. እነሆ፤ ባሪያዬ የሚያከናውነው በማስተዋል ነው፤ገናና ይሆናል፤ ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግ ይከብራልም።

14. ብዙዎች በእርሱ እስኪደነግጡ ድረስ፣መልኩ ከማንም ከሰው የተለየ፤ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ።

15. ስለዚህ ብዙ መንግሥታትን ያስደንቃል፤በእርሱ ምክንያት ነገሥታት አፋቸውን ይይዛሉ፤ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ያልሰሙትን ያስተውላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 52