ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 51:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ተድላና ደስታ፣ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በእርሷ ይገኛሉ።

4. “ወገኔ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ሕዝቤ ሆይ፤ ስማኝ፤ሕግ ከእኔ ይወጣል፤ፍርዴም ለሕዝቦች ብርሃን ይሆናል።

5. ጽድቄ በፍጥነት እየቀረበ፣ማዳኔም እየደረሰ ነው፤ክንዴም ለመንግሥታት ፍትሕን ያመጣል፤ደሴቶች ወደ እኔ ይመለከታሉ፤ክንዴንም በተስፋ ይጠብቃሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 51