ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 50:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤በየማለዳው ያነቃኛል፤በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።

5. ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም።

6. ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢሜን ለሚነጩ ጒንጬን ሰጠሁ፤ፊቴን ከውርደት፣ከጥፋትም አልሰወርሁም።

7. ልዑል እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይአድርጌአለሁ፤እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።

8. ንጹሕ መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ በአጠገቤ አለ፤ታዲያ ማን ሊከሰኝ ይችላል?እስቲ ፊት ለፊት እንጋጠም!ተቃዋሚዬስ ማን ነው?እስቲ ይምጣ!

9. የሚረዳኝ እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤የሚፈርድብኝስ ማን ነው?እነሆ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ብልም ይበላቸዋል።

10. ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው?ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤በአምላኩም ይደገፍ።

11. አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ።እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤በሥቃይም ትጋደማላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 50