ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 49:14-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ጽዮን ግን፣ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ጌታም ረስቶኛል” አለች።

15. “እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን?ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን?ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣እኔ ግን እልረሳሽም።

16. እነሆ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ቅጥሮችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።

17. ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ፤ያፈራረሱሽም ከአንቺ ይሸሻሉ።

18. ዐይንሽን ቀና አድርጊ፤ ዙሪያውንም ተመልከቺ፤ወንዶች ልጆችሽ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ።“በሕያውነቴ እምላለሁ፤እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊያቸዋለሽ” ይላል እግዚአብሔር።

19. “ፈራርሰሽ ባድማ ብትሆኚ፣ምድርሽ ፈጽሞ ቢጠፋ፣ዛሬ ለሕዝብሽ ጠባብ ብትሆኚም እንኳ፣የዋጡሽ ከአንቺ ይርቃሉ።

20. በሐዘንሽ ዘመን የወለድሻቸው ልጆች፣ጆሮሽ እየሰማ፣‘ይህ ቦታ በጣም ጠቦናል፤የምንኖርበት በቂ ስፍራ ስጪን’ ይሉሻል።

21. በልብሽም እንዲህ ትያለሽ፣‘እነዚህን የወለደልኝ ማን ነው?እኔ ሐዘንተኛና መካን፣የተሰደድሁና የተጠላሁ ነበርሁ፤እነዚህን ማን አሳደጋቸው?ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ታዲያ፣ እነዚህ ከየት መጡ?’

22. ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ አሕዛብን በጥቅሻ እጣራለሁ፤ዐርማዬንም ለሕዝቦች ከፍ አደርጋለሁ፤ወንዶች ልጆችሽን በዕቅፋቸው ያመጡልሻል፤ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ይሸከሙልሻል።

23. ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ፣እቴጌዎቻቸው ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤የእግርሽን ትቢያ ይልሳሉ፤አንቺም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቂያለሽ፤እኔን ተስፋ የሚያደርጉም አያፍሩም።”

24. ከተዋጊ ብዝበዛ ማስጣል፣ከጨካኝስ ምርኮኞችን ማዳን ይቻላልን?

25. እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤“ከተዋጊዎች ላይ ምርኮኞች በርግጥ ይወሰዳሉ፤ከጨካኞችም ላይ ምርኮ ይበዘበዛል፤ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፤ልጆችሽንም እታደጋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 49