ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 43:16-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በባሕር ውስጥ መንገድ፣በማዕበል ውስጥ መተላለፊያ ያበጀ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

17. እንደ ገና ላይነሡ እዚያው እንዲተኙ፣እንደ ጧፍ ኵስታሪ ረግፈው እንዲጠፉ፣ሠረገሎችንና ፈረሶችን፣ሰራዊቱንና ደጀኑን በአንድነት ያወጣ እንዲህ ይላል፤

18. “የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ያለፈውን እርሱ።

19. እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን?በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤

20. የምድረ በዳ አራዊት፣ቀበሮና ጒጒት ያከብሩኛል፤በምድረ በዳ ውሃ፣በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁና።ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ እሰጣለሁ፤

21. ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብምስጋናዬን ያውጅ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ።

22. “ያዕቆብ ሆይ፤ አንተ ግን አልጠራኸኝም፤እስራኤል ሆይ፤ የእኔ ነገር ታክቶሃል።

23. ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎች አላመጣህልኝም፤በመሥዋዕትህም አላከበርኸኝም።በእህል ቍርባን አላስቸገርሁህም፤በዕጣን መሥዋዕትም አላሰለቸሁህም።

24. መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን አልገዛህልኝም፤በመሥዋዕትህ ሥብ አላጠገብኸኝም፤ነገር ግን የኀጢአት ሸክምህን ጫንህብኝ፤በበደልህም አደከምኸኝ።

25. “ስለ ራሴ ስል መተላለፍህን የምደመስ ስልህ፣እኔ፣ እኔው ነኝ፤ኀጢአትህን አላስባትም።

26. እስቲ ያለፈውን አስታውሰኝ፤ተቀራርበን እንከራከርበት፤ትክክለኛ ስለ መሆንህም አስረዳ።

27. የመጀመሪያው አባትህ ኀጢአት ሠርቶአል፤መምህሮችህም ዐምፀውብኛል።

28. ስለዚህ የመቅደስህን አለቆች አዋርዳለሁ፤ያዕቆብን ለጥፋት፣እስራኤልን ለስድብ እዳርጋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 43