ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 41:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “ከምሥራቅ አንዱን ያነሣው፣በጽድቅም ወደ አገልግሎቱ የጠራው ማን ነው?አሕዛብን አሳልፎ ሰጠው፤ነገሥታትን በፊቱ አስገዛለትበሰይፉም እንደ ትቢያ አቦነናቸው፤በቀስቱም በነፋስ እንደ ተበተነ ገለባ አደረጋቸው።

3. አሳደዳቸው ያለ ችግር ዐልፎ ሄደ፤እግሩም ቀድሞ ባልረገጠው መንገድ ተጓዘ።

4. ይህን የሠራና ያደረገ፣ትውልድን ከጥንት የጠራ ማን ነው?እኔ እግዚአብሔር ከፊተኛው፣ከኋለኛውም ጋር፤ እኔው ነኝ።”

5. ደሴቶች አይተው ፈሩ፤የምድር ዳርቾች ደነገጡ፤ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ።

6. እያንዳንዱ ይረዳዳል፤ወንድሙንም፣ “አይዞህ” ይለዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 41