ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 40:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ያዕቆብ ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትላለህ?እስራኤል ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትናገራለህ?“መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፤ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ?

28. አታውቅምን?አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው።አይደክምም፤ አይታክትም፤ማስተዋሉም በማንም አይመረመርም።

29. ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ለዛለው ጒልበት ይጨምራል።

30. ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፤ ይታክታሉም፤ጐበዛዝትም ተሰናክለው ይወድቃሉ።

31. እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ኀይላቸውን ያድሳሉ፤እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 40