ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 38:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በአካዝ የሰዓት መቍጠሪያ ደረጃ ላይ፣ የወረደውን የፀሓይ ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።’ ” ስለዚህ ወርዶ የነበረው የፀሓይ ጥላ ያንኑ ያህል ወደ ኋላ ተመለሰ።

9. የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከሕመሙ ከተፈወሰ በኋላ የጻፈው ጽሕፈት፤

10. እኔ፣ “በዕድሜዬ እኩሌታ፣በሲኦል ደጆች ማለፍ አለብኝን?የቀረውንስ ዘመኔን ልነጠቅ ይገባልን?” አልሁ።

11. እንዲህም አልሁ፤ “ዳግም እግዚአብሔርን፣ እግዚአብሔርን በሕያዋን ምድር አላይም፤ከእንግዲህም የሰውን ዘር አላይም፤በዚህ ዓለም ከሚኖሩትም ጋር አልሆንም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 38