ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 38:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ ታመመ፤ ሞት አፋፍ ደረሰ፤ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ መጥቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ ትሞታለህና ቤትህን አሰናዳ’ ” አለው።

2. ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳ አዙሮ፣ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤

3. “እግዚአብሔር ሆይ፤ በፊትህ በታማኝነትና በፍጹም ልብ ደስ የሚያሰኝህንም በማድረግ እንዴት እንደኖርሁ አቤቱ አስብ።” ሕዝቅያስም አምርሮ አለቀሰ።

4. የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 38