ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 34:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።

5. ሰይፌ በሰማያት እስኪበቃት ጠጥታለች፤እነሆ፤ ወደ ኤዶም፣ፈጽሞ ወዳጠፋሁት ሕዝብ ለፍርድ ወርዳለች።

6. የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ሥብ ጠግባለች፤በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቶአልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 34