ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 28:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፣በለመለመ ሸለቆ ዐናት ላይ ጒብ ብላ፣የክብሩ ውበት ለሆነች ጠውላጋ አበባ፣የወይን ጠጅ ለዘራቸው መኵራሪያ ለሆነች፣ለዚያች ከተማ ወዮላት!

2. እነሆ፤ ጌታ ኀያልና ብርቱ የሆነ ነገር አለው፤ይህም እንደ በረዶ ወጀብ፣ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስ፣እንደ ኀይለኛ ማዕበል፣ እንደ ከባድ ዝናብ፣በኀይል ወደ ምድር ይጥላታል።

3. የኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል፣በእግር ይረገጣል።

4. በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጒብ ብላ፣የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋትወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።

5. በዚያን ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ለተረፈው ሕዝቡ፣የክብር ዘውድ፣የውበትም አክሊል ይሆናል።

6. እርሱም በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጠው፣የፍትሕ መንፈስ፣ጦርን ከከተማዪቱ በር ላይ ለሚመልሱም፣የኀይል ምንጭ ይሆናል።

7. እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገደገዱ፤በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ።

8. የማእድ ገበታቸው ሁሉ በትፋት ተሞልቶአል፤ከትውኪያም የጸዳ ቦታ የለም።

9. እነርሱም እንዲህ ይላሉ፤ “የሚያስተምረው ማንን ነው?መልእክቱን የሚያብራራውስ ለማን ነው?ወተት ለተዉት ሕፃናት?ወይስጡት ለጣሉት?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 28