ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 23:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ፤ጢሮስ ተደምስሳለችና፤ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች።ከቆጵሮስ ምድር፣ዜናው ወጥቶላቸዋል።

2. እናንት የባሕር ተጓዦች ያበለጠጓችሁ፣በደሴቲቱ የምትኖሩ፣የሲዶና ነጋዴዎችም ጸጥ በሉ።

3. በታላላቅ ውሆች ላይ፣ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤የዐባይ መከር ገቢዋ ነበር፤እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች።

4. አንቺ ሲዶና ሆይ፣አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፣ ዕፈሪ፤ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሎአልና።

5. ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣በግብፅ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።

6. እናንት በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 23