ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 22:15-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሂድና ይህን መጋቢ፣የቤቱንም ኀላፊ ሳምናስን እንዲህ በለው፤

16. ‘እዚህ ምን ታደርጋለህ?በዚህ ስፍራ ለራስህ መቃብርን እንድ ታዘጋጅ፣በከፍታውም ላይ መቀበሪያህን እንድ ትወቅር፣ሬሳህ የሚያርፍበትንም ዐለት እንድ ትጠርብ ማን ፈቀደልህ?’

17. አንተ ኀያል ሰው ሆይ፤ ተጠንቀቅ፤ እግዚአብሔር አጥብቆ ሊይዝህ፣ በእጆቹም ጨብጦ ሊወረውርህ ነው።

18. አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረበዚያ ትሞታለህ፤የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ።

19. ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ከኀላፊነትህም ትባረራለህ።

20. “በዚያን ቀን አገልጋዬን፣ የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፤

21. መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።

22. የዳዊትን ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 22