ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 2:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል።እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ።ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።

5. እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ።

6. የያዕቆብ ቤት የሆነውን፣ሕዝብህን ትተሃል፤እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ከባዕዳን ጋር አገና ይማታሉ።

7. ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ሀብታቸውም ልክ የለውም።ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም።

8. ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ጣቶቻቸው ላበጇቸው፣ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ።

9. ሰው ዝቅ ብሎአል፤የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል።

10. ከእግዚአብሔር አስፈሪነት ከግርማው ሽሽ፤ወደ ዐለቶች ሂድ፤በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

11. የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።

12. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣የተኵራራውን በሙሉየሚያዋርድበት ቀን አለው።

13. ረዥምና ከፍ ከፍ ያሉትን የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ፣የባሳንን የወርካ ዛፎች ሁሉ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 2