ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 19:9-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የተነደፈ የተልባ እግር የሚፈትሉ፣የተባዘተ ጥጥ የሚሠሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቈርጣሉ።

10. ልብስ ሠሪዎች ያዝናሉ፤ደመወዝተኞችም ልባቸው ይሰበራል።

11. የጣኔዎስ አለቆች በጣም ሞኞች ናቸው፤የፈርዖን ጠቢባን ምክራቸው የማይረባ ነው፤ፈርዖንን፣ “እኔ ከጥበበኞች አንዱ ነኝ፤የጥንት ነገሥታትም ደቀ መዝሙር ነኝ”እንዴት ትሉታላችሁ?

12. የእናንተ ጠቢባን አሁን የት አሉ?የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርበግብፅ ላይ ያሰበውን ነገር፣እስቲ ያሳዩአችሁ፤ ያሳውቋችሁም።

13. የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤የሜምፊስ ሹማምት ተታለዋል፤የሕዝቧ ዋና ዋናዎች፣ግብፅን አስተዋታል።

14. እግዚአብሔር የድንዛዜን መንፈስ አፍሶባቸዋል፤ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ፣ግብፅንም በምታደርገው ነገር ሁሉእንድትንገዳገድ አደረጓት።

15. ራስም ይሁን ጅራት፣ የዘንባባ ዝንጣፊም ይሁን ደንገል፣ለግብፅ የሚያደርጉላት አንዳች ነገር የለም።

16. በዚያን ቀን ግብፃውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ካነሣው ክንዱ የተነሣ በፍርሀት ይንቀጠቀጣሉ።

17. የይሁዳ ምድር በግብፅ ላይ ሽብር ትነዛለች፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ካቀደው የተነሣ፣ ስለ ይሁዳ፣ ወሬ የሰማ ሁሉ ይሸበራል።

18. በዚያ ቀን አምስት የግብፅ ከተሞች በከነዓን ቋንቋ ይናገራሉ፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርም ወገን ለመሆን ቃል ኪዳን ይገባሉ፤ ከእነዚህም ከተሞች አንዲቱ የጥፋት ከተማ ተብላ ትጠራለች።

19. በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለእግዚአብሔር ዐምድ ይቆማል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 19