ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 17:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. በዚያ ቀን ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ይመለከታሉ፤ዐይኖቻቸውም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።

8. በእጃቸውም ወደ ሠሯቸው መሠዊያዎች አይመለከቱም፤በጣቶቻቸው ላበጇቸው የዕጣን መሠዊያዎች፣ለአሼራም የአምልኮ ዐምዶችክብር አይሰጡም።

9. በዚያን ቀን በእስራኤል ልጆች ምክንያት የተተውት ጠንካራ ከተሞች ጥሻና ውድማ እንደሆኑ ሁሉ፣ እነዚህ ሁሉ ባድማ ሆናሉ።

10. አዳኝ አምላክህን ረስተሃል፤መሸሸጊያ ዐለትህንም አላስታወስህም፤ስለዚህ ምርጥ ተክል ብትተክልም፣እንግዳ ዘርንም ብትዘራ፣

11. በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣በዘራህበትም ማግሥት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣እንዳልነበረ ይሆናል።

12. አቤት፤ የብዙ ሕዝቦች የቍጣ ድምፅእንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል፤አቤት፤ የሰዎች ከፍተኛ ጩኸት!እንደ ኀይለኛ ውሃ ያስገመግማል።

13. ሰዎቹ እንደ ኀይለኛ ውሃ ጩኸት ቢያስገመግሙም፣እርሱ ሲገሥጻቸው፣በኰረብታ ላይ በነፋስ እንደሚበን ትቢያ፣በዐውሎ ነፋስ ፊት እንደሚበተን ገለባ ይበተናሉ።

14. እነሆ፤ ሲመሽ ድንገተኛ ሽብር ሆነ!ከመንጋቱ በፊት ግን አንዳቸውም አልተገኙም።የዘረፉን ዕድል ፈንታ፣የበዘበዙን ዕጣ ይህ ሆነ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 17