ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 17:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ደማስቆ የተነገረ ንግር፤“እነሆ፤ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማነቷ ይቀራል፤የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።

2. የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤የሚያስፈራቸውም የለም።

3. የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤የሶርያም ቅሬታእንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

4. “በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይደበዝዛል፤የሰውነቱም ውፍረት ይሟሽሻል።

5. አጫጅ የቆመውን ሰብል ሰብስቦ፣ዛላውንም በክንዱ እንደሚያጭድ፣ይህም በራፋይም ሸለቆእንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።

6. ሆኖም የወይራ ዛፍ ሲመታ፣ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በቅርንጫፍ ራስ ላይ እንደሚቀር፣አራት ወይም አምስት ፍሬም ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚቀር፣እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይተርፋል”ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።

7. በዚያ ቀን ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ይመለከታሉ፤ዐይኖቻቸውም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 17