ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 16:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከምድረ በዳው ማዶ ካለችው ከሴላ፣ለምድሪቱ ገዥ፣ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራየበግ ጠቦት ግብር ላኩ።

2. ከጐጆአቸው ተባርረውግራ እንደ ተጋቡ ወፎች፣የሞዓብ ሴቶችምበአርኖን ወንዝ መሻገሪያ እንዲሁ ይሆናሉ።

3. “ምክር ለግሱን፤ውሳኔ ስጡን፤በቀትር ጥላችሁንእንደ ሌሊት አጥሉብን፤የሸሹትን ደብቁ፤ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ።

4. የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋር ይቈዩ፤እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።”የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ጥፋቱ ያከትማል፤እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል።

5. ዙፋን በፍቅር ይመሠረታል፤ከዳዊት ቤት የሆነ፣በፍርድ ፍትሕን የሚሻ፣ጽድቅንም የሚያፋጥን፣አንድ ሰው በታማኝነት በላዩ ይቀመጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 16