ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 14:25-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. አሦርን በምድሬ ላይ አደቃለሁ፤በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ቀንበሩ ከሕዝቤ ላይ ይነሣል፤ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”

26. ለምድር ሁሉ የታሰበው ዕቅድ ይህ ነው፤በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይኸው ነው።

27. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቦአል፤ማንስ ያግደዋል?እጁም ተዘርግቶአል?ማንስ ይመልሰዋል?

28. ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት እንዲህ የሚል ንግር መጣ፤

29. “እናንት ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል።

30. ከድኻም ድኻ የሆኑት መሰማሪያ ያገኛሉ፤ችግረኞችም ተዝናንተው ይተኛሉ፤ሥርህን ግን በራብ እገድላለሁ፤ትሩፋንህንም እፈጃለሁ።

31. በር ሆይ፣ ዋይ በል፤ ከተማ ሆይ ጩኽ፣ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ ሁላችሁም በፍርሀት ቅለጡጢስ ከሰሜን መጥቶብሃል፤ከሰልፉ ተነጥሎ የሚቀር የለምና።

32. ከዚያ ሕዝብ ለሚመጡ መልእክተኞች ምን መልስ ይሰጣል?መልሱ፣ “እግዚአብሔር ጽዮንን መሥርቶአል፤መከራን የተቀበለው ሕዝብም፣በእርሷ ውስጥ መጠጊያን አግኝቶአል” የሚል ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 14